ውድ ወላጆች
ይህ የ2ኛ ክፍል የአካባቢ ሳይንስ ትምህርት የኢትዮጵያን ሥርዓተ ትምህርት መስፈርቶች ጠብቆ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ተማሪዎች ስለ አካባቢ፣ የሰው አካል፣ ሀይል፣ የአየር ሁኔታ እና የፀሐይ ስርዓት ማራኪ በሆኑ ቪዲዮዎች እና ተግባራዊ ሙከራዎች ታግዘው ይማራሉ። ትምህርቱ ልጆች ሳይንሳዊ፣ ማህበራዊ እና አጠቃላይ ግንዛቤን (እንደ ጤና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የባህል ብዝሃነት እና የመንገድ ደህንነት ያሉ ጉዳዮችን) በዕለት ተዕለት ሕይወታቸው እንዲተገብሩ ለማስቻል ያለመ ሲሆን፤ የተማሪዎች የትምህርት አቀባበልም በየክፍለ ትምህርቱ በሚሰጡ አጫጭር ፈተናዎች፣ በምዕራፍ መጨረሻ ግምገማዎች፣ እና በመጨረሻ ፈተና አማካኝነት ይለካል።
Curriculum
- 7 Sections
- 29 Lessons
- 360 Days
Expand all sectionsCollapse all sections
- ምዕራፍ አንድ፡ የወረዳችን መገኛ6 Items
- ምዕራፍ ሁለት፡ ሳይንስን መገንዘብ4 Items
- ሲሚስተር 1፡ ማጠቃለያ እና ፈተና2 Items
- ምዕራፍ ሦስት፡ ተፈጥሮአዊ አካባቢ6 Items
- ምዕራፍ አራት፡ ማኅበራዊ አካባቢ6 Items
- ምዕራፍ አምስት፡ ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች3 Items
- ሲሚስተር 2፡ ማጠቃለያ እና ፈተና2 Items
Instructor

Eskedar Kebede
ሰላም! እኔ እስከዳር ከበደ እባላለሁ፤ በህክምና ሳይንስ ዘርፍ ያለኝን እውቀት ከተማሪዎች ስኬት ጋር በማጣመር፣ ውስብስብ ትምህርቶችን በቀላሉ፣ በተግባር የተደገፉ እና ሳቢ በሆነ መልኩ በማቅረብ ላይ እሰራለሁ። ለተማሪዎች አሰልቺ ያልሆነ እና በራስ መተማመንን የሚገነባ የመማር ልምድ ለመፍጠር፣ ለወላጆች ደግሞ የልጆቻቸውን ሂሳዊ አስተሳሰብ የሚያሳድግ ጥራት ያለው የትምህርት ይዘት ለማቅረብ በትጋት እሰራለው። ሁላችንም በጋራ በመሆን ተማሪዎቻችን በፈተናዎቻቸውም ሆነ በወደፊት ህይወታቸው የላቀ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እናብቃቸው!
