ውድ ወላጆች፣
ይህ የ8ኛ ክፍል የአማርኛ ትምህርት ተማሪዎች የቋንቋ እውቀታቸውን በማጠናከር ወደ ጥልቅ ትንተና የሚሸጋገሩበት ኮርስ ነው።
የትምህርቱ ዋና ዓላማ የልጆችን የንባብ፣ የፅሁፍ፣ የማዳመጥና የመናገር ክህሎቶች ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግና ማዳበር ነው። በንባብና ፅሁፍ የተለያዩ ጽሑፎችን በጥልቀት መመርመር፣ የተዋቀሩ ድርሰቶችን መጻፍና የቃላት ሀብትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ይደረጋል። በማዳመጥና መናገር ደግሞ ሀሳብን በራስ መተማመን በቃል ማቅረብን እንዲሁም ውስብስብ ሰዋስው መገንባትን ይለማመዳሉ።
እነዚህን ግቦች ማሳካት ተማሪዎች በአማርኛም ሆነ በሌሎች ትምህርቶች እንዲሁም በህይወታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ያግዛቸዋል።
የተማሪዎችን የትምህርት ሂደትና ውጤታማነት ለመከታተል የተለያዩ ተከታታይ እና አጠቃላይ የግምገማ ዘዴዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ። ከነዚህም ውስጥ በእያንዳንዱ ትምህርት መጨረሻ የሚሰጡ አጫጭር ፈተናዎች እና በይነተገናኝ የክፍል ውስጥ እንቅስቃሴዎች ይገኙበታል። በተጨማሪም የተማሪዎችን አጠቃላይ ግንዛቤ ለመለካት የምዕራፍ መጨረሻ ግምገማዎች እና የዓመቱ የመጨረሻ (የሚኒስትሪ) ፈተና ይሰጣቸዋል።
Curriculum
- 10 Sections
- 60 Lessons
- 365 Days
Expand all sectionsCollapse all sections
- 1. የሥራ ሥነ ምግባር6 Items
- 2. ባህላዊ ቅርስ6 Items
- 3. ሰብዓዊ እሴቶች6 Items
- 4. አጭር ልቦለድ6 Items
- 5. ሥነ-ሕዝብ6 Items
- 6.በረሃማነት6 Items
- 7. የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ6 Items
- 8. ሰላም6 Items
- 9. የአየር ንብረት6 Items
- 10. ተውኔት6 Items
Instructor
