አማርኛ ሁለተኛ ክፍል 10 Sections41 Lessons365 Days
ምዕራፍ አንድ ማጠቃለያ
Freedom Learning | የ2ኛ ክፍል ማጠቃለያ
አማርኛ አጭር ማጠቃለያ (Cheatsheet)
ምዕራፍ 1
1
ቃላት እና ሰዋሰው
👕 የልብስ አይነቶች
- ✓ ቀሚስ: ለሴቶች የሚሆን ባህላዊ ወይም ዘመናዊ ልብስ፡፡
- ✓ ነጠላ: ከጥጥ የሚሰራ ነጭ የባህል ልብስ፡፡
- ✓ ጋቢ: ለብርድ ጊዜ የሚለበስ ወፍራም የባህል ልብስ፡፡
- ✓ ሱሪ: ከወገብ በታች የሚለበስ ልብስ፡፡
- ✓ ጫማ: ለእግር መከላከያ የምናደርገው፡፡
- ✓ ኮት: ከሸሚዝ ላይ የሚለበስ ልብስ፡፡
1 ነጠላ – “ይህ”
አንድን ነገር ወይም ልብስ ብቻ ለማመልከት እንጠቀምበታለን::
👉 ይህ ቀሚስ ነው:: 👗
👉 ይህ ሸሚዝ ነው:: 👕
👉 ይህ ጃኬት ነው:: 🧥
2+ ብዙ – “እነዚህ”
ከአንድ በላይ የሆኑ ልብሶችን ወይም ነገሮችን ለማመልከት እንጠቀምበታለን::
👉 እነዚህ ጫማዎች ናቸው:: 👞👞
👉 እነዚህ ሱሪዎች ናቸው:: 👖👖
👉 እነዚህ ካልሲዎች ናቸው:: 🧦