አማርኛ አምስተኛ ክፍል 12 Sections54 Lessons365 Days
1.5. ምዕራፍ አንድ ማጠቃለያ
ፍሪደም ለርኒንግ
የ5ኛ ክፍል የአማርኛ ማጠቃለያ
ምዕራፍ 1 – አጭር ማጠቃለያ
ማዳመጥ፣ ንባብ፣ ቃላት፣ ሰዋስው
የአንቀጽ አወቃቀር
አንቀጽን የሚያዋቅሩ ዓረፍተነገሮች
-
ኃይለ ቃል
የአንቀጹን ዋና ሀሳብ የሚይዝ መሠረታዊ ዓረፍተነገር ነው።
-
መዘርዝራዊ ዓረፍተነገሮች
ኃይለ ቃሉን የሚያብራሩና የሚደግፉ ዝርዝር ዓረፍተነገሮች ናቸው።
ሰዋስው፡ የስም አይነቶች
ስም ምንድን ነው?
በዓረፍተነገር ውስጥ በባለቤትነትና በተሳቢነት የሚያገለግል የቃል ክፍል ነው።
በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባል፡
- ✓ የወል ስም
- ✓ የተጸውኦ ስም
ዝርዝር የስም ክፍሎች
1. የወል ስም
ተመሳሳይ ተፈጥሮ ያላቸው ነገሮች በጋራ የሚጠሩበት የጋራ ስያሜ።
ምሳሌ፡ በሬ፣ ተራራ፣ ወንዝ
2. የተጸውኦ ስም
ለአንድ ግለሰብ ወይም ነገር ብቻ የሚሰጥ የግል መጠሪያ።
ምሳሌ፡ ማክቤል፣ አባይ፣ ኢትዮጵያ
የክለሳ ጥያቄዎች
ከተማራችሁት በመነሳት ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ስጡ፡፡
“ጓደኛ መሆን” በሚለው ምንባብ ውስጥ በአንደኛው እና በሁለተኛው አንቀጾች ውስጥ የሚገኙትን ኃይለ ቃልና መዘርዝራዊ ዓረፍተነገሮችን አውጥታችሁ አሳዩ።
ቀጥሎ የቀረቡትን ስሞች የወል ወይም የተጸውኦ ስም መሆናቸውን ለይታችሁ አመልክቱ፡፡